የልብና የደም ዝውውር ህመም

የልብና የኩላሊት ህመም የሚይዘው ማን ነው?

የስኳር ህመም፣ከፍተኛ የደም ግፊት፣የኩላሊት ህመም፣ከፍተኛ የደም ኮሌስትሮል፣ቤተሰብ ውስጥ በ ወጣትነት በልብ ህመም የተያዘ ሰው ካለ ሲጋራ ማጨስ፤ ከመጠን በላይ ውፍረት፤ የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ፤ ከ 45 ዐመት በላይ የሆነው ወንድ እና ከ 55 ዐምት በላይ የሆናት ሴት::

ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ በልብ ህመም የመያዝን እድል ከፍ ያረጉታል።

የኩላሊት ህመም እና የልብ ህመም እንዴት ይገናኛሉ

ልባችሁና ኩላሊታችሁ የተገናኙና አንዳቸው ለሌላው ጥገኛ ናቸው ። እንዲሁም ለልብ ህመምም ሆነ ለኩላሊት ህመም የሚያዳርጉ ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ ችግሮች አሉ። ከእነዚህም መካከል

የስኳር ህመም-በስኳር ህመም ጊዜ በደም ውስጥ ከመጠን በላይ ግሉኮስ (ወይም ስዃር) ይገኛል። በደም ውስጥ ያለው ግሉኮስ ልብንና ኩላሊትን ጨምሮ ብዙ የሰውነትን ክፍሎች ሊጎዳ ይችላል ።

ከፍተኛ የደም ግፊት-የደም ግፊት ደም በደም ቱቦዎች (ወይም ደም ሥሮች) ግድግዳ ላይ የሚገፋበት ኃይል ነው ።ከፍተኛ የደም ግፊት በሚኖርበት ጊዜ ልብ ደምን በሰውነት ውስጥ ለማዘዋወር ይበልጥ ይከብደዋል ፤ ይህ ደግሞ ልብን ሊያደክም ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ፡ ከፍተኛ የደም ግፊት የደም ሥሮችን ሊጎዳ ይችላል። ከፍተኛ የደም ግፊት በኩላሊት ውስጥ ያሉ ትንንሽ የደም ሥሮችን የሚጎዳ ከሆነ ኩላሊቶች ደምን የሚገባውን ያህል አያጣሩም።ኩላሊት ሲጎዳ ከሰውነት ውስጥ ከመጠን በላይ ወይም አላስፈላጊ ውኃና ጨውን አጣርቶ ለማስወገድ ሊሳነው ይችላል።በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የደም ግፊት የኩላሊት ህመምን ሊያባብስ ይችላል።  

 

የኩላሊት ህመምእና የልብ ህመምን መከላከል ይቻላል?

ሁሌም የኩላሊት ህመም እና የልብ ህመምን መከላከል ባይቻልም የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውሰድ ለኩላሊት ህመም እና ለልብ ህመም የመጋለጥ እድሉን መቀነስ ይቻላል። የደም ግፊትዎን ከ140/90 በታች ማድረግ የስኳር ህመም ያለባቸው የደም ግሉኮሳቸውን መቆጣጠር። የኮሌስትሮል ቁጥርዎን በጤናማ ክልል ውስጥ ለማቆየት መሞከር። ክብደትን መቆጣጠርና ጤናማ ምግብ መመገብ።በሳምንትውስጥ አብዛኛውን ቀን ቢያንስ 30 ደቂቃ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ።

አብዛኞቹ የሰውነታችን ክፍሎች ጠንካራ ትስስር ያላቸው ከመሆኑም አንዳቸው ለሌላው ላይ ጥገኛ ናቸው። የልብና የኩላሊት ሁኔታም ቢሆን ከዚህ የተለየ አይደለም ። በኩላሊት ህመምና በልብና በደም ሥሮች ህመም መካከል ጠንካራ ግንኙነት አለ ።

የስኳር ህመም ምንድን ነው?

የኩላሊት ችግር ዋነኛ መንስኤ የስኳር ህመም ነው። በብዙ አገሮች ዳያሊሲስ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት በስኳር ህመም ምክንያት የኩላሊት ችግር ያለባቸው ናቸው። 

በስኳር ህመም ምክንያት የሚመጣ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም(Diabetic Nephropathy) ይባላል።የስኳር ህመም ካለ በደም ውስጥ በጣም ብዙ ግሉኮስ (ስኳር) አለ። በደም ውስጥ ያለው ግሉኮስ ልብንና ኩላሊትን ጨምሮ ብዙ የሰውነትን ክፍሎች ሊጎዳ ይችላል።በተጨማሪም የስኳር ህመም ያለባቸው ብዙ ሰዎች ከፍተኛ የደም ግፊት ያድርባቸዋል። የኩላሊት ህመም ዋነኛ መንስኤዎች ከፍተኛ የደም ግፊትና የስኳር ህመም እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ።

የስኳር የኩላሊት ህመም (Diabetic nephropathy) የመያዝ ዕድላቸው ከፍ ያለ ማን ነው?

ለረጅም ጊዜ የስኳር ህመም ያለባቸው ሆነው በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በጣም ከፍተኛ ሲሆን የስኳር ህመም ያለባቸው ሆነው የደም ግፊታቸው በጣም ከፍተኛ የሆኑ የስኳር ህመም ያለባቸው ሲጋራ አጫሾች አካላዊ እንቅስቃሴ የማይሰሩ ከመጠን በላይ ወፍራም የሆኑየልብ ህመም ያለባቸው የኩላሊት ችግር በቤተሰብ ውስጥ ያላቸው::

የስኳር ህመም ካለብህ/ካለብሽ ኩላሊትን ጤናማ ለማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

ከስኳር ህመም ጋር የተያያዙ የኩላሊት ህመምዎችን ለማዘግየት ወይም ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መንገድ የደም ግሉኮስን እና የደም ግፊት መቆጣጠር ነው። ጤናማ የአኗኗር ልማዶች እና የታዘዘውን መድሃኒቶችዎን በአግባቡ መውሰድ የደም ግሉኮስና የደም ግፊትን ለመቆጣጠር እና በአጠቃላይ ጤንነትዎን ለማሻሻል ይረዳዎታል::

 • የደም ግሉኮስ ግቦችዎ ላይ መድረስ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ በአማካይ የደም ግሉኮስ መጠንዎን ለማየት A1C የደም ምርመራ ያድርጉ. የኤ1ሲ ቁጥርህ በበዛ መጠን ባለፉት 3 ወራት ውስጥ የደም ግሉኮስዎ መጠንም የበዛ ነበር ማለት ነው። የስኳር ህመም ያለባቸው ብዙ ሰዎች ኤ1ሲ የተባለው ግብ ከ7 በመቶ በታች ነው ። የጤና ባለሙያን የ A1C ግብዎ ምን መሆን እንዳለበት ይጠይቁ ።
 • የደም ግፊትዎን ይቆጣጠሩ
 • ከፍተኛ የደም ግፊት የልብ ድካም፣ በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስና የኩላሊት ህመም ሊያስከትል ይችላል። ለአብዛኛዎቹ የስኳር ህመምተኞች የደም ግፊት ግብ ከ ከ140/90 ሚሊሜትር Hg በታች ነው። የጤና ባለሙያዮን ግብዎ ምን መሆን እንዳለበት ይጠይቁ። የደም ግፊትን የሚቀንሱ መድሃኒቶችም የኩላሊት ጉዳትን ለመቀነስ ይረዳሉ። የኩላሊት ችግር ዋነኛ መንስኤ የስኳር ህመም ነው። በብዙ አገሮች ዳያሊሲስ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት በስኳር ህመም ምክንያት የኩላሊት ችግር ያለባቸው ናቸው። በስኳር ህመም ምክንያት የሚመጣ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም(Diabetic Nephropathy) ይባላል።የስኳር ህመም ካለ በደም ውስጥ በጣም ብዙ ግሉኮስ (ስኳር) አለ። በደም ውስጥ ያለው ግሉኮስ ልብንና ኩላሊትን ጨምሮ ብዙ የሰውነትን ክፍሎች ሊጎዳ ይችላል።በተጨማሪም የስኳር ህመም ያለባቸው ብዙ ሰዎች ከፍተኛ የደም ግፊት ያድርባቸዋል። የኩላሊት ህመም ዋነኛ መንስኤዎች ከፍተኛ የደም ግፊትና የስኳር ህመም እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ። የስኳር የኩላሊት ህመም (Diabetic nephropathy) የመያዝ ዕድላቸው ከፍ ያለ ማን ነው? ለረጅም ጊዜ የስኳር ህመም ያለባቸው ሆነው በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በጣም ከፍተኛ ሲሆን የስኳር ህመም ያለባቸው ሆነው የደም ግፊታቸው በጣም ከፍተኛ የሆኑ የስኳር ህመም ያለባቸው ሲጋራ አጫሾች አካላዊ እንቅስቃሴ የማይሰሩ ከመጠን በላይ ወፍራም የሆኑየልብ ህመም ያለባቸው የኩላሊት ችግር በቤተሰብ ውስጥ ያላቸው
 • •ጤናማ የአኗኗር ልማድ አዳብሩ ወይም ኑሩ ጤናማ የአኗኗር ልማዶች የደም ግሉኮስና የደም ግፊት ግቦች ላይ ለመድረስ ሊረዱህ ይችላሉ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደረጃዎች መከተልም ኩላሊትዎ ጤናማ እንዲሆን ይረዳዎታል
 •  የስኳር ህመም የምግብ እቅድ ለማዘጋጀት እና ጨው እና ሶዲየም ገድብ ከአመጋገብ ባለሙያ ጋር መስራት ማጨስ አቁም
 • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
 • የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ክፍል እንዲሆን አድርጉ።
 • ጤናማ ክብደት ይኑርዎ።
 • በቂ እንቅልፍ ይኑርዎ ።
 • በየቀኑ ማታ ከ7 እስከ 8 ሰዓት ለመተኛት ግብ አኑሩ።
 • መድሃኒቶችዎን በአግባቡ ይውሰዱ ለጉንፋን ወይም ለትኩሳት የሚሆኑ ብዙ መድኃኒቶች በኩላሊትዎ ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ስለዚህ ስለምትወስዷቸው መድሃኒቶች ሁሉ ከጤና ባለሙያዎ ወይም ከፋርማሲስትዎ ጋር ይነጋገሩ

ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት (AKI)

በኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የኩላሊት አሰራር ላይ ተፅእኖ ያመጣል. አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማለትም በቀናት ውስጥ ሊክሰት ይችላል በአብዛኛውን ጊዜ ኩላሊቱ ከሞላ ጎደል ከድገተኛ የኩላሊት ድካም (AKI) ሙሉ በሙሉ ይድናል፣ ነገር ግን ኩላሊቶቹ እንዲያገግሙ በመጠባበቅ ላይእያለ አፋጣኝ ህክምናን ዳያሊስስን ጨምሮ ሊያስፈልግ ይችላል።ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት (AKI በመባል የሚታወቀው) ቀደም ብሎ ከተገኘ፣ ሙሉ በሙሉ የኩላሊት ድካም ከመከሰቱ በፊት ሕክምናው ኩላሊቶቹ በፍጥነት እንዲያገግሙ ያስችላቸዋል::

ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት (AKI) መንስኤው ምንድን ነው

ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት (AKI) ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉት። በድንገት ወደ ኩላሊቶች የሚፈስሰው የደም መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ።በአንዳንድ መድኃኒቶች፣ መርዞች ወይም ኢንፌክሽኖች ምክንያት የሚደርስ ጉዳት።ሽንቱ ከኩላሊት እንዳይወጣ የሚያግድ ድንገተኛ መዘጋት።

በሚከተሉት የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል በኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የመድረስ እድሉ ሰፊ ነው

 • በዕድሜ የገፉ
 • የኩላሊት ወይም የጉበት ህመም፣ የስኳር ህመም፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ድካም ወይም ከልክ
  ያለፈ ውፍረት የመሳሰሉ የረጅም ጊዜ የጤና ችግር ያለባችው።
 • በጠና የታመሙ፤የልብ ወይም የሆድ ቀዶ ሕክምና ወይም መቅኒ ወደ ሌላ ቦታ መተካት የኩላሊት ጉዳት
  ሊያስከትሉ ይችላሉ።

የኩላሊት አደጋ ምልክቶች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ :-

 • ትንሽ ብቻ ወይም ምንም ሽንት አለመሽናት.
 • የሰውነት ማበጥ በተለይ የእግር እብጠት።
 • የምግብ ፍላጎት መቀነስ ።
 • የማቅለሽለሽ ስሜትና ማስመለስ።
 • ግራ መጋባት፣ መጨነቅ፤ መቁነጥነጥ ወይም እንቅልፍ ማጣት።

የደም ግፊት (Hypertension) ምንድን ነው

ለአብዛኞቹ ሰዎች 140/90 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ የደም ግፊት ከፍተኛ እንደሆነ ይታሰባል የደም ግፊት በደም ሥሮች ግድግዳ ላይ የሚገፋኃይል ኃይል ነው ። Hypertension የሕክምና ቃል ሲሆን ይህም ደም በሰውነት ውስጥ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ በደም ሥሮች ላይ የሚያደርሰው ንዑስ ኃይል መጠን መጨመር ማለት ነው።የደም ግፊት ምርመራ ውጤት ሲጻፍ ሁለት ቁጥሮች በህዝባር ተለያይተው ነው (ለምሳሌ 140/90)። የመጀመሪያው ቁጥር ሲስቶሊክ የደም ግፊት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የልብ ምት በሚመታበት ጊዜ ያልውን የደም ግፊት ይለካል፤ ሁለተኛው ቁጥር ዳያስቶሊክ (diastolic) የደም ግፊት ሲባል ልብ በምት መካከል በሚያርፍበት ጊዜ በደም ሥሮች ውስጥ ያለውን ግፊት ይለካል።

ለአብዛኛዎቹ ሰዎች 120/80 የደም ግፊት የተለመደ ሲሆን ከ140/90
በላይ የሆነ ማንኛውም ውጤት ደግሞ ጤናማ እንዳልሆነ (ከፍተኛ
የደም ግፊት) ተደርጎ ይቆጠራል።

የልብ ህመም ምንድን ነው?

የልብ ህመም ልብዎን ደም ከማዘዋወር የሚያግዱ ማንኛውንም ችግሮችን ያካትታል። ችግሩ የሚጀምረው በደም ሥሮች ወይም በልብ ውስጥ ሊሆን ይችላል ። የልብና የደም ሥሮች ችግሮች ከዚህ በታች የተጠቀስቱን ያካትታሉ፦ በደም ሥሮች ግድግዳ ላይ ፕላክ (plaque) የተባለ ንጥረ ነገር መገንባት ወደ ልብ የሚፈሰውን የደም ዝውውር የሚያግድ የደም መርጋት የልብ ድካም – ማለትም በደም ና በኦክሲጅን እጥረት ምክንያት የሚከሰት የልብ ጉዳት

የደም ግፊት እና የኩላሊት ህመም መካከል ያለው ግንኙነት

የደም ግፊት የኩላሊት ህመም ሊያስከትል የሚችል ከመሆኑም በላይ በብዙ አገሮች የኩላሊት
ችግር ዋነኛ መንስኤ ነው። ከፍተኛ የደም ግፊት በኩላሊቶች ውስጥ የሚገኙ የደም ሥሮችን
በመጉዳት በተገቢው መንገድ የመስራት ችሎታቸውን ሊቀንስ ይችላል። በኩላሊቶቹ ውስጥ ያሉት የደም ሥሮች ጉዳት የደረሰባቸው ከሆነ ቆሻሻና ተጨማሪ ፈሳሽ ከሰውነት ውስጥ ማስወገዱን ሊያቆሙ ይችላሉ። በደም ሥሮች ውስጥ ተጨማሪ ፈሳሽ መኖሩ የደም ግፊቱን ይበልጥ ከፍ ሊያደርግና አደገኛ ዑደት ሊያስከትል ይችላል። ይሁን እንጂ በተዘዋዋሪ የኩላሊት ህመም ከፍተኛ የደም ግፊትንም ሊያስከትል ይችላል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ከፍተኛ የደም ግፊት ኩላሊቶቹ በፍጥነት እንዲበላሹ ያደርጋል።

ከፍተኛ የደም ግፊት እና የኩላሊት ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የደም ግፊት የመጀመሪያ ምልክቶች ባይኖሩትም የልብ፣ የዓይንና የኩላሊት ጉዳትን ጨምሮ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ህመምና የጤና እክል ሊያስከትል ይችላል። ጉዳቱ ሳይታወቅ ለበርካታ ዓመታት ቀስ በቀስ ሊከሰት ይችላል ። አንዳንድ ጊዜ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ራስ ምታት ሊያጋጥማቸው ይችላል። በተጨማሪም የኩላሊት ህመም ገና ከጅምሩ ምልክቶች አይኖሩትም። አንድ ሰው ከፍተኛ የደም ግፊተንዳለበት ለማወቅ በተደጋጋሚ የደም ግፊት ምርመራ ይከናወናሉ። ምርመራው በየጊዜው ከ140/90 ከፍተኛ የደም ግፊት መኖሩን ያረጋግጣል። አንድ ሰው የኩላሊት ህመም እንዳለበት የሽንትእና የደም ምርመራ ይሰራለታል::

የደም ግፊትና የኩላሊት ህመምን መከላከል ወይም ማዘግየት ይቻላል?

የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ የኩላሊት ህመምን ለመቀነስ ወይም ለመከላከል ይረዳል። የደም ግፊትን መቆጣጠር የሚቻለው በመድሀኒት እንዲሁም ቀላል የአኗኗር ለውጥ በማድረግ ነው።

የአኗኗር ለውጥ የሚከተሉትን ያካትታል

-ጤናማ አመጋገብ አካላዊ እንቅስቃሴ ጤናማ ክብደት መያዝ ማጨስ ማቆም በመድኃኒትና በአኗኗር ለውጥ የደም ግፊትን መቆጣጠር ኩላሊትን ከተጨማሪ ጉዳት ለመጠበቅ ይረዳል። ለዚህም ነው ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ለኩላሊት ህመም ምርመራ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው።