ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ሰዎች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ተቀባይነት የሌለው፣ ፍትሃዊ ያልሆነ ብሎም እየጨመረ ያለ ነው።

 

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በዓለም ላይ ቁጥር 1 ሞት እና የአካል ጉዳት መንስኤዎች ናቸው። ምንም እንኳን በአብዛኛው አስቀድሞ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፣ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚመዘገቡት ሞቶች 74% እና ከዓለም አካል ጉዳተኞች ግማሹን ያህል በመንስዔነት ይሸፍናሉ።

አሁን ላይ፣ በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ የሰዎች ሞት በተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ምክንያት ይከሰታል። ይህ ቁጥር በ2030 ወደ 52 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል።

ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ላይ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የግንዛቤ ማስጨባጫ ሳምንት።

Global Week for Action on NCDs!

 

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ዋነኛ የሰብአዊ መብቶች እና ፍትሃዊነት ጉዳይ ናቸው - ከሁሉም በላይ ደግሞ በበቂ ሁኔታ በገንዘብ ያልተደገፉ የዓለም ጤና ችግሮች ናቸው።

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በጣም ድሃ ብሎም በጣም ተጋላጭ ህዝብ በሚኖርባቸው ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ውስጥ የድህነት፣ እና ተመጣጣኝ ያልሆነ ጫና ዋነኛ መንስኤ (ብሎም መዘዝ) ናቸው።

 

በሰዎች፣ በጤና ስርዓቶች፣ በኢኮኖሚዎች ላይ ከሚኖረው ዘላቂ የረጅም ጊዜ ተፅዕኖ እና ከተጎዱት በቢሊዮኖች ከሚቆጠሩ ሰዎች አንፃር ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በጣም ዝቅተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው የዓለም የጤና ጉዳዮች ናቸው። የኢንቨስትመንት ክፍተቱን ማቃለል በ2030 ህይወትን ለማዳንና ለማሻሻል ለዓለም ታላቅ እምቅ አቅምን ይሰጣል፤ እንዲሁም ከ30-70 ዕድሜ ክልል ባሉ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ላይ በአመት እስከ 15 ሚሊዮን የሚደርሱ በተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ከሚከሰቱት ሞቶች አብዛኞቹን መከላከል ወይም ማዘግየት ይቻላል ተብሎ ይታሰባል።

 

ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ላይ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የግንዛቤ ማስጨባጫ ሳምንት።

መንግስታት ድፍረት የተሞላበት እንቅስቃሴን በማድረግ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማሳካት ይችላሉ።

በ2030 በተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች የሚመጣውን ያለጊዜ ሞትን በአንድ ሶስተኛ ለመቀነስ የኤስ.ዲ.ጂ. (SDG) ግብ 3.4 ላይ መድረስ ወጪ ቆጣቢ እና ተጨባጭ ነው። በ2023 እና 2030 መካከል የዓለም ጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች የበጀታቸውን 20% ብቻ ከፍተኛ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ጥቅም ላይ ካዋሉ 39 ሚሊዮን ህይወትን ማዳን ይቻላል።

 

የአለም ጤና ድርጅት የምርጥ ግዢዎችን (Best Buys) ትግበራን ጨምሮ በተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ላይ ድፍረት የተሞላበት እንቅስቃሴ በማድረግና እርምጃ በመውሰድ ብሄራዊ መንግስታት በአጭር እና በረጅም ጊዜ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማግኘት ይችላሉ።


ይህንን ለማሳካት ጤናን እንደ ወጪ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢንቨስትመንትም ማየት ይጠይቃል። በተጨማሪም እንደ ብዙ የፋይናንስ ምንጮችን መጠቀምና ለተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ፈጠራ መፍትሄዎች የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ የረዥም ጊዜና ከሳጥን ውጪ የሆኑ አስተሳሰቦችን ማራመድ ያስፈልጋል።


ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ላይ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የግንዛቤ ማስጨባጫ ሳምንት።

የዓለም ኢኮኖሚዎች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ችላ ለማለት አይችሉም።

የዓለም ኢኮኖሚዎች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ችላ ለማለት አይችሉም።

 

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች የዓለምን ኢኮኖሚ ያሟጥጣሉ፣ በሰው ኃይል አቅም ላይ ሃይለኛ ስጋት ይፈጥራሉ፣ እንዲሁም ድህነትን በቤተሰብ እና በማህበረሰቦች ውስጥ ያራዝማሉ።

 

በአጠቃላይ አምስቱ መሪ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች – የልብና የደም ቧንቧ ህመም፣ ሥር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት ህመም፣ ካንሰር፣ የስኳር ህመም እና የአዕምሮ ጤና ሁኔታዎች – ከ2011 እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ከዓለም ኢኮኖሚ እስከ 47 ትሪሊዮን ዶላር በየዓመቱ እንደሚያስወጡ ይገመታል። ይህ በእንዲ እንዳለ የተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ህክምና ወጪዎች በየዓመቱ የሚሊዮኖችን ኪስ በማራቆት ወደ ከፋ ድህነት እየገፏቸውም ይገኛሉ።

 

ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ላይ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የግንዛቤ ማስጨባጫ ሳምንት።

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች የመቋቋም አቅም፣ የወረርሽን ዝግጁነት እና የጤና ስርዓቶች ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ።

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ላይ የሚታየው የእንቅስቃሴ ጉድለት እና የገንዘብ ድጋፍ እጥረት ሕይወትንና ኢኮኖሚን ብቻ አይደለም የሚጎዳው፣ የጤና ደህንነትን በመቀነስ አገሮች ለወደፊት ወረርሽኞችና የጤና ስጋቶች ያላቸውን የምላሽ ዝግጁነት ላይም ከባድ ተጽዕኖ ያሳድራል።

 

ከ60% እስከ 90% የሚሆነው የኮቪድ-19 ሞት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በነበረባቸው ሰዎች ላይ ነበር የተመዘገበው። ለጤና ከሚውለው የልማት ዕርዳታ ውስጥ ለተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ከ1-2 በመቶ ላይ ብቻ ሆኖ ለሁለት አስርት ዓመታት በመቆየቱና ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችና አጋላጭ መንስኤዎቻቸው ላይ እርምጃ ባለመወሰዱ ህዝቡን፣ የጤና ስርአቶችን እና ኢኮኖሚውን ኮቪድ-19ን ጨምሮ ለተለያዩ ወረርሽኞች ዋና ተጽኖዎች የመጋለጥ እድላቸውን ከፍ ያደረገው መሆኑ ታይቷል።