ሴቶች እና የኩላሊት ህመም

የኩላሊት ህመም በሁሉም እድሜ እና ዘር ላይ ያሉ ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል። ነገር ግን ሴቶች ከኩላሊት ህመም ጋር የተያያዙ ልዩ ተግዳሮቶችን ያጋጥማቸዋል። ሴቶች በሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም (ሲኬዲ) የመያዝ ዕድላቸው ከወንዶች እኩል ወይም ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። ሲኬዲ በዓለም ዙሪያ በግምት 195 ሚሊዮን ሴቶችን ያጠቃል እና በአሁኑ ጊዜ በሴቶች ላይ 8 ኛው ግንባር ቀደም የሞት ምክንያት ነው ፣ በግምት በየዓመቱ 600,000 ሰዎችን ይገድላል። ሲኬዲ ለሌሎች ህመምዎች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል እና በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ወደ ኩላሊት ውድቀት ይመራል። ታማሚዎች እዚህ ድረስ ከደረሱ የኩላሊት መተኪያ ሕክምናን (የኩላሊት እጥበት ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ) ይፈልጋሉ

ለሴቶች ልዩ ፈተናዎች ምንድን ናቸው?

መፀነስ:- CKD የመራባት አቅምን ለመቀነስ ትልቅ ምክንያት ተደርጎ ይቆጠራል። በተለይም በመጨረሻው ደረጃ ላይ ዳያሊስስ በሚያስፈልግበት ጊዜ። በዳያሊስስ ላይ ያለች ሴት የመውለድ ችሎታ ፈታኝ ሊሆን ቢችልም ሊደረግ የሚችል ነው እናም ውጤቶቹ በከፍተኛ ህክምና ከታገዙ (በየቀኑ ወይም በአማካይ በየቀኑ) ይሻሻላሉ።

ለሴቶች ልዩ ፈተናዎች ምንድን ናቸው?

ሁለቱም አጣዳፊ
የኩላሊት ጉዳት(AKI) እና ፕሪኤክላምፕሲያ (PE) ወደ CKD እድገት
ሊመሩ ይችላሉ።ፕሪኤክላምፕሲያ የእርግዝና ውስብስብነት ሲሆን
በእትብት ደም እጥረት ወይም በእናቶች ህመምዎች ምክንያት የሚከሰት
እና በእናቲቱ ላይ የደምግፊት እና የኩላሊት ጉዳት የሚያስከትል ነው። 

 

በእናቶች ጤና ላይ ብቻ ሳይሆን በፅንሱ ውስጥ በማህፀን ውስጥ መሞት ቅድመ ወሊድ እና የተገደበ የማህፀን እድገት ጋር ሊያስከትል ይችላል።በእናቲቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም ዓይነት የኩላሊት ህመም በእርግዝና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል እናም በእናቲቱ እና በፅንሱ ጤና ላይ አደጋ ሊያስከትል ይችላል። CKD ባለባቸው ሴቶች ብዙ አሉታዊ የእርግዝና ውጤቶች ( እንደ ፕሪኤክላምፕሲያ፣ AKI፣ CKD እድገት፣ ድንገተኛ ፅንስ ማስወረድ፣ ፅንስ ማስወረድ፣ መወለድ፣ የአካል ጉድለቶች እና ሌሎች የረጅም ጊዜ ጉዳዮች) የመከሰታቸው እድል የጨመረ ነው።

በሴቶች ላይ ምን ዓይነት የኩላሊት ህመምዎች በብዛት ይገኛሉ?

ሉፐስ ኔፍሪቲስ (ኤል.ኤን.) በኤስ.ኤል.ኢ (ሲስቴሚክ ሉፐስ ኤራይቲማቶሰስ) የሚመጣ የኩላሊት ጉዳት ነው። ይህ ህመም የሰውነታችን ህመም የመከላከል ስርዓት ጤነኛ የሆኑ ሕብረ ሕዋሳትን የሚያጠቃበት ህመም ነው። በሉፐስ ምክንያት የሚመጣ የኩላሊት ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ሄዶ ወደ ኩላሊት ውድቀት ሊያመራ ይችላል። ሉፐስ ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ በጣም የተለመደ ሲሆን ብዙውን ጊዜ በወሊድ ጊዜ ይመታል። ሉፐስ ካለባቸው 10 ሰዎች ዘጠኙ ሴቶች ናቸው።የኩላሊት ኢንፌክሽን (ፓይሎኔፍራይቲስ) በአብዛኛው በባክቴሪያ የሚከሰት እና ከታችኛው የሽንት ቱቦ ውስጥ የሚጀምር ኢንፌክሽን ሲባባስ የሚከተል ነው። የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ካልታከመ ወደ ላይ ወደ አንዱ ወይም ሁለቱም ኩላሊቶች ይሸጋገራል። የኩላሊት ኢንፌክሽኖች ወደ የተሰራጨ ኢንፌክሽን ሊመራ ይችላል፤ ይህም ለሕይወት አስጊ ነው። በአካሎቻቸው ምክንያት ሴቶች እና ልጃገረዶች ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተጋለጡ ናቸው።

የጤና እንክብካቤ መዳረሻ:

ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሴቶችን ደህንነት ሊነኩ ይችላሉ። ህጋዊ ፅንስ ማስወረድ በማይቻልባቸው አገሮች ውስጥ ከሕገ-ወጥ ፅንስ ማስወረድ በኋላ የሚከሰት የተሰራጨ ኢንፌክሽን የ AKI ዋነኛ መንስኤ። ውስብስቦቹ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ሴቶች ላይ ከፍተኛ ናቸው። አለም አቀፋዊ እና ወቅታዊ የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ በቂ ባለማግኘት ፣ ፕሪኤክላምፕሲያ ያለባቸውን ሴቶች ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እና ለከባድ AKI እጥበት ባለማግኘት ምክንያትም ነው። 

 

የኩላሊት መተካት ሕክምና (RRT) ማግኘት (እጥበት እና ንቅለ ተከላ ጨምሮ) በብዙ ማህበረሰቦች ውስጥ ላሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች አሳሳቢ ሊሆን ይችላል። ሴቶች በብዛት የኩላሊት ለጋሾች ቢሆኑም፣ በሚፈልጉበት ጊዜ የመቀበል ዕድላቸው ግን አነስተኛ ነው።በ 2018 የአለም የኩላሊት ቀን መሪ ሃሳብ “የሴቶች እና የኩላሊት ህመምዎች” ነበር። ከሴቶች እና ተላላፊ ያልሆኑ ህመምዎች ግብረ ኃይል ጋር በመተባበር የአለም የኩላሊት ቀን በ”ኩላሊት ህመም እና ሴቶች” ላይ የፖሊሲ ሰነድ አዘጋጅቷል::

 

መግለጫው በኩላሊት ህመም እና በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ የኩላሊት ህክምና ተደራሽነት እና የኩላሊት ህመምን በመከላከል ረገድ ያሉ ወቅታዊ ማስረጃዎችን እና ቁልፍ ተግዳሮቶችን ያጎለበተ ሲሆን እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ተጨባጭ የፖሊሲ ምክሮችን አስቀምጧል።እንዲሁም እዚህ በ2018 የአለም የኩላሊት ቀን ምክንያት የተጻፈ ሳይንሳዊ አርታኢ ማንበብ ይችላሉ:- ስለ ሴቶች እና የኩላሊት ህመምዎች የምናውቀው እና የማናውቀው፤ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እና ያልተመረመሩ መልሶች፤ በአለም የኩላሊት ቀን እና በአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ላይ የተደረገ ውይይት። 

የአካል ክፍል ለጋሽ ምን አይነት ዘላቂ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?

ከለጋሽ እና ታካሚ ማዛመድ በስተጀርባ ያሉ የአሰራር ዝርዝሮች እና ፖሊሲዎች ከአገር ወደ ሀገር
ይለያያሉ። ይሁን እንጂ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙት የፊዚዮሎጂ መስፈርቶች ተመሳሳይ ናቸው።
ብዙውን ጊዜ ግምት ውስጥ የሚገቡት ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ::

 

የደም ዓይነት ፡- የተቀባዩ እና የለጋሹ የደም አይነት ተስማሚ መሆን አለበት። የሰው ነጭ የደም ህዋስ አንቲጂኖች (HLA) ፡- እነዚህ አንቲጂኖች የሰውነትዎን ሕብረ ሕዋሳት እና የውጭ ንጥረ ነገሮችን የመለየት ኃላፊነት ያላቸው ፕሮቲኖች ናቸው። 

ክሮስ-ተዛማጅ አንቲጂኖች፡- ንቅለ ተከላ ከመደረጉ በፊት የሚደረግ ሙከራ ነው። የተቀባዩ እና የለጋሽ ደም ትንሽ ናሙናዎች ይቀላቀላሉ። ከዛም ምንም ምላሽ ካልተከሰተ ንቅለ ተከላው ሊቀጥል ይችላል ማለት ነው።

          እያንዳንዱ የአካል ክፍል ልገሳ ለተቸገረ ሰው የሕይወት ስጦታ ነው።

በአንዳንድ ሁኔታዎች የቦታው ርቀት ግምት ውስጥ ይገባል። ምክንያቱም አንዳንድ የአካል ክፍሎች ከ 6 ሰአታት በላይ ከሰውነት ውጭ ሊኖሩ ስለማይችሉ ነው። ለምሳሌ ኩላሊት ከሰውነት ውጭ የሚቆይበት አማካይ ጊዜ 30 ሰአት ነው።

 

ከበሽተኛው ጋር የመመሳሰል እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ አብዛኛው የህያው ልገሳ የሚደረገው በቤተሰብ አባላት ነው። ነገር ግን የህመም መከላከያ መድሃኒቶች መስፋፋት ምክንያት ለጋሽ እና ተቀባይ የግድ የደም ዘመድ መሆናቸው አያስፈልግም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበርካታ በጎ አድራጊ ለጋሾች እና የተጣመሩ ልገሳዎች ጨምረዋል። ስለ ሕያው ልገሳ እቅዶች በህያው ለጋሾች አውታረ መረብ ድህረ ገጽ ላይ የበለጠ ማንበብ ይችላሉ።

የአካል ክፍሎች ለጋሾች እነማን ናቸው?

ሁለት አይነት ለጋሾች አሉ፤ በህይወት ያሉ እና የሞቱ ለጋሾች።
በህይወት ያለ ለጋሽ:- የአካል ክፍሎችን ለመለገስ ፈቃደኛ የሆነ ጤናማ ሰው ነው። ብዙውን ጊዜ በህይወት
ያሉ ለጋሾች ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው እና የአካል ክፍሎችን ለመለገስ ፈቃደኛ የሆነ ሰው መሆን አለበት።
ከልገሳ በኋላ በህይወታቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ እና አንድምታ እንዲረዱም በአእምሯቸው
ሆነም በአካላቸው በርካታ የሆኑ የጤና ግምገማዎች ይደረግባቸዋል::

 

የሞቱ ለጋሾች:– የአካል ክፍሎቻቸውን ለመለገስ ያላቸውን ፍላጎት የገለጹ ሟች ናቸው። ብዙ ሰዎች የሞቱ ለጋሾች ለመሆን ቢመዘገቡም የተወሰኑት ብቻ ናቸው ተስማሚ የሚሆኑት። የሞተው ለጋሽ አንጎሉ የሞተ መሆን አለበት። አብዛኛዎቹ የሞቱ ለጋሾች የአንጎል አኔሪዝም/ስትሮክ ታማሚዎች ወይም ከባድ የጭንቅላት ጉዳት ያለባቸው ታካሚዎች ናቸው

ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና የኩላሊት ህመም

ከመጠን በላይ መወፈር ለብዙ የጤና ችግሮች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል የስኳር ህመም፣ የልብና የደም ሥር ህመም፣ የደም ግፊት፣ የኩላሊት ህመም፣ እና ሌሎችም ጨምሮ። እስከ 2025 ከመጠን ያለፈ ውፍረት 18% ወንዶች እና 21% የሚሆኑ ሴቶችን በዓለም ዙሪያ ይጎዳሉ። በአንዳንድ ሀገራት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከአንድ ሶስተኛ በላይ በሆነው የጎልማሳ ህዝብ ላይ ይገኛል እና ለአጠቃላይ ጤና እና ለከፍተኛ አመታዊ የህክምና ወጪዎች ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ከመጠን ያለፈ ውፍረት ምንድን ነው?

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ከመጠን ያለፈ ውፍረትን “ጤና ሊጎዳ የሚችል ያልተለመደ ወይም ከመጠን በላይ የሆነ የስብ ክምችት” ሲል ይገልፃል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት አብዛኛውን ጊዜ በሰውነት ብዛት ማውጫ (BMI) ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የእርስዎን BMI ለማግኘት ክብደትዎን (በኪሎግራም) በከፍታዎ(በሜትር) ሁለት ጊዜ ያካፍሉት። ለአዋቂዎች BMI ከ18.5 እስከ 25 ኪ.ግ/ሜ.2 ከሆነ በWHO እንደ መደበኛ ክብደት ይቆጠራል። ከ 25 እስከ 29.9 ኪ.ግ / m2 መካከል ያለው BMI ከመጠን በላይ ክብደት እናም ከ 30 ኪ.ግ / m2 በላይ የሆነ BMI እንደ ከመጠን በላይ ውፍረት ይቆጠራል። ለልጆችና ጎልማሶች የተለያዩ የመለያ ነጥቦች ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ልብ ሊባል ይገባል።ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዴት እንደሚለካ የበለጠ ዝርዝር መረጃ በአለም ውፍረት ፌዴሬሽን ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ። በኩላሊት ህመም እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? ከመጠን በላይ ውፍረት ባላቸው ሰዎች ላይ የኩላሊት ህመም የመከሰቱ አጋጣሚ ከፍተኛ ነው። የስኳር ህመም እና የደም ግፊት ያለባቸውን ጨምሮ። በተጨማሪም በተዘዋዋሪ መንገድ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለዋና ዋና የCKD ስጋት ምክንያቶች (2ተኛ ዓይነት የስኳር ህመም እና የደም ግፊት መጨመርን) ያስከስታል። ቀጥተኛ መንስኤው ደግሞ ኩላሊቶች ከመጠን በላይ ውፍረት ባላቸው ሰዎች ላይ የጨመረው ሜታቦሊዝም ፍላጎቶችን ለማሟላት ከመደበኛው ደረጃ በላይ በማጣራት ጠንክሮ መሥራት አለባቸው። ይህ የተግባር መጨመር ለረጅም ጊዜ ሲኬዲ የመያዝ እድሉ ከፍተኛ ያደርገዋል። ከመጠን በላይ ክብደት ያላቸው ሰዎች ለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት (AKI) ተጋላጭ ናቸው። AKI በድንገት የሚያድግ፣ ብዙ ጊዜ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እና ዋናው መንስኤው ከታከመ በኋላ ሙሉበሙሉ ሊጠፋ የሚችል ከባድ ህመም ነው፣ነገር ግን ህይወት ዘላቂ ችግሮች ሊያስከትል ይችላል። ከመጠን ያለፈ ውፍረትን መከላከል እና/ወይም መታከም ይቻላል? ክብደትን በአስተማማኝ እና በጤናኛ (ከተቻለ) ለመቀነስ አንዳንድ መንገዶች እዚህ አሉ። • ክብደትን በአስተማማኝ እና በጤናኛ (ከተቻለ) ለመቀነስ አንዳንድ መንገዶች እዚህ አሉ። • ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ጡንቻን የሚያጠናክር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (እንደ ፑሽ አፕ ወይም ሲት አፕ) • ጤናማ አመጋገብ እና መጠን መቆጣጠር • በአንዳንድ ሁኔታዎች የቤሪያትሪክ (ክብደት መቀነስ) ቀዶ ጥገና አማራጭ ሊሆን ይችላል። ከመጠን በላይ መወፈርን ለመከላከል ሶስት ቀላል እርምጃዎችን መውሰድ አለብዎት፡- • ከጠቅላላዎ ስብ እና ስኳር የኃይል ፍጆታን ይገድቡ • ትኩስ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ፍጆታ ይጨምሩ • በመደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስሪት። ለህፃናት በቀን 60 ደቂቃዎች እና ለአዋቂዎች 150 ደቂቃዎች በሳምንቱ ውስጥ ይሰራጫሉ። በ 2017 የዓለም የኩላሊት ቀን ትኩረት “የኩላሊት ህመም እና ውፍረት” ነበር። ያለፉ የዘመቻ ቁሳቁሶችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ። የአለም የኩላሊት ቀን ከአለም አቀፍ ውፍረት ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የጋራ አቋም አዘጋጅቷል። ሰነዱ ስለ የኩላሊት ህመም፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ተያያዥነት ያላቸውን አንዳንድ ቁልፍ መረጃዎችን ያጠቃለለ ሲሆን፥ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና የኩላሊት ህመምን ለመከላከል መንግስታት እና ፖሊሲ አውጪዎች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ጥቂት ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን ያካትታል። በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ከመጠን በላይ መወፈርን መከላከል ይቻላል። ሊታከምም ይችላል። ብዙውን ጊዜ ችግሩ በአኗኗር ለውጦች ሊፈታ ይችላል። ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ በሽተኛው ክብደትን ለመቀነስ የሕክምና እርዳታ ሊፈልግ ይችላል። ከመጠን በላይ ወፍራም ከሆኑ የሰውነት ክብደት 5 በመቶውን ብቻ መቀነስ ለብዙ ህመምዎች የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል። ቀስ ያለ እና ቋሚ ክብደት መቀነስ በጣም አስተማማኝ መንገድ ነው። ከ 0.5 እስከ 1.4 ኪሎግራም በሳምንት እናም በሳምንት ከ 3 ኪሎ ግራም ያልበለጠ ክብደትን ለመቀነስ ማለም ይመከራል።

ከመጠን ያለፈ ውፍረትን መከላከል እና/ወይም መታከም ይቻላል

ክብደትን በአስተማማኝ እና በጤናኛ (ከተቻለ) ለመቀነስ አንዳንድ መንገዶች እዚህ አሉ።

  • ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ጡንቻን የሚያጠናክር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (እንደ ፑሽ አፕ
    ወይም ሲት አፕ)
  • ጤናማ አመጋገብ እና መጠን መቆጣጠር
  • በአንዳንድ ሁኔታዎች የቤሪያትሪክ (ክብደት መቀነስ) ቀዶ ጥገና አማራጭ ሊሆን ይችላል።

ከመጠን በላይ መወፈርን ለመከላከል ሶስት ቀላል እርምጃዎችን መውሰድ አለብዎት::

  • ከጠቅላላዎ ስብ እና ስኳር የኃይል ፍጆታን ይገድቡ
  • ትኩስ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ፍጆታ ይጨምሩ
  • በመደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስሪት። ለህፃናት በቀን 60 ደቂቃዎች እና ለአዋቂዎች 150
    ደቂቃዎች በሳምንቱ ውስጥ ይሰራጫሉ።

በ 2017 የዓለም የኩላሊት ቀን ትኩረት “የኩላሊት ህመም እና ውፍረት” ነበር። ያለፉ የዘመቻ ቁሳቁሶችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ። የአለም የኩላሊት ቀን ከአለም አቀፍ ውፍረት ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የጋራ አቋም አዘጋጅቷል። ሰነዱ ስለ የኩላሊት ህመም፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ተያያዥነት ያላቸውን አንዳንድ ቁልፍ መረጃዎችን ያጠቃለለ ሲሆን፥ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና የኩላሊት ህመምን ለመከላከል መንግስታት እና ፖሊሲ አውጪዎች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ጥቂት ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን ያካትታል::

በኩላሊት ህመም እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?

ከመጠን በላይ ውፍረት ባላቸው ሰዎች ላይ የኩላሊት ህመም የመከሰቱ አጋጣሚ ከፍተኛ ነው። የስኳር ህመም እና የደም ግፊት ያለባቸውን ጨምሮ። በተጨማሪም በተዘዋዋሪ መንገድ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለዋና ዋና የCKD ስጋት ምክንያቶች (2ተኛ ዓይነት የስኳር ህመም እና የደም ግፊት መጨመርን) ያስከስታል። ቀጥተኛ መንስኤው ደግሞ ኩላሊቶች ከመጠን በላይ ውፍረት ባላቸው ሰዎች ላይ የጨመረው ሜታቦሊዝም ፍላጎቶችን ለማሟላት ከመደበኛው ደረጃ በላይ በማጣራት ጠንክሮ መሥራት አለባቸው። ይህ የተግባር መጨመር ለረጅም ጊዜ ሲኬዲ የመያዝ እድሉ ከፍተኛ ያደርገዋል። ከመጠን በላይ ክብደት ያላቸው ሰዎች ለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት (AKI) ተጋላጭ ናቸው። AKI በድንገት የሚያድግ፣ ብዙ ጊዜ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እና ዋናው መንስኤው ከታከመ በኋላ ሙሉበሙሉ ሊጠፋ የሚችል ከባድ ህመም ነው፣ነገር ግን ህይወት ዘላቂ ችግሮች ሊያስከትል ይችላል።